በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የበርሊን ኤምባሲ የሚሰጥ የቆንስላ አገልግሎት

መግቢያ

 • ባለጉዳዮች ወደ በርሊን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኮንሱላር አገልግሎት በምትመጡበት ወቅት የተሟላ ሰነድ እና በቂ የሰነድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እያሳወቅን ፣ ይህን በማሟላት ከመጣችሁ በኋላ ኮፒ ፍለጋ ላለመንከራተት እንዲሁም ጊዜያችሁን በአግባቡ ለመጠቀም ይረዳል፡፡

 • እንዲሁም መረጃዎቻችሁን በፖስታ የምትልኩ ባለጉዳዮች መረጃችሁን ወደ እናንተ መልሰን የምንልከው የመመለሻ ፖስታ ጨምራችሁ በምትልኩ ጊዜ ብቻ መሆኑን እናሳውቃልን፡፡

 • ከፌቡራሪ 2023 ጀምሮ የወጣው አዲስ የኮንሱላር አገልግሎት የዋጋ ታሪፍ

 • በሚስዮኑ የቆንስላ ክፍል ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሰጥ ዋና ዋና የአገልግሎት ዓይነት ሰነድ አልባ፣ቀድሞ የነበራቸውን ፓስፖርት ይፈለግልኝ ፣ የድጋፍ ደብዳቤ ፣ የሰነድ ማረጋገጥና የውክልና አገልግሎት ናቸው፡፡
 • ከላይ የተጠቀሰውን አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልግ ፎቶግራፍ ስፋቱ 3 x 4 ሴ.ሜ የሆነ፣ የሰውነት ክፍል በመቀስ ያልተነካ (ባዮሜትሪክ) ፣ ከስድስት ወር ወዲህ በከለር የተነሱት፣ ሁለቱ ጀሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለ፣ ከጀርባው ስም የተፃፈበት 4 ፎቶ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
 • ለፓስፖርትና ለትውልድ ኢትዮጵያዊ የሚያስፈልግ አሻራ ለመስጠት ወደ ኤምባሲው መምጣት የማይችሉ የቼክ፣ ስሎቫክና ፖላንድ ነዋሪዎች በአካባቢዎ ለሚገኝ ፖሊስ አሻራውን በመስጠት በፓብሊክ ኖታሪና በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር በማረጋገጥ መላክ ይኖርበታል፡
 •  ከዚህ ቀደም አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም፡፡
 • እድሜአቸው ከ 14 አመት በታች የሆኑ ህፃናት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም፡፡
 •  አገልግሎቱን ለመውሰድ የሚያስፈልጉ የአገልግሎት መጠየቂያ ቅፆች፣ የውክልና መስጫ ቅፆች፣ የአሻራ መውሰጃ ቅፅ ከየአገልግሎቱ ዓይነት ጋር ተያይዘው ይገኛሉ፡፡
 •  በአካል መምጣት የማይችሉ ወይም የማይገባዎት ከሆነና የአገልግሎት ጥያቄዎትን በፖስታ ቤት በኩል ከላኩ አገልግሎቱ ከሶስት ቀን እስከ የአንድ ሳምንት ጊዜ ሊፈጅ ይችላል፡፡
 • ማመልከቻውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ቴምብር የተለጠፈበትና የላኪ አድራሻ በትክክል የተፃፈበት መልሶ መላኪያ ፖስታ መላክ ይኖርብዎታል፡፡

Commerzbank  Berlin

Account No. – 2673978          IBAN:   DE31 1004 0000 0267397800

BLZ –10040000                      Swift Code (BIC): COBADEFFXXX

 • ሚስዮኑ የኦንላይን የክፍያ አሰራር የጀመረ በመሆኑ ለፈጣን አገልግሎት የOnline Banking System መጠቀም ይችላሉ፡፡
 • በምንሰጠው አገልግሎት ቅሬታና አስተያየት ካለዎት በድህረ-ገፃችን በተዘጋጀው የአስተያየት መስጫ ቅፅ ላይ በመሙላት እንዲያቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ (ቅፁን ለማግኘት ከዚህ ይጫኑ)

ማሳሰቢያ፡ ..  ፌብሯሪ 28 ቀን 2017 ጀምሮ ከታሪፍ በላይ እና በስህተት ገቢ የተደረገ ገንዘብ ተመላሽ የማናደርግ መሆናችንን ከይቅርታ ጋር እናሳውቃለን።